15.The Rock 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾችና ገላጭ ከኾነው ቁርኣን ናት፡፡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡፡ ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ (ጊዜያት) ያላት ኾና እንጂ አላጠፋንም፡፡ ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜዋን ምንም አትቀድምም፡፡ (ከእርሱ) አይቆዩምም፡፡ «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡ «ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት (መስካሪ) ለምን አትመጣንም» (አሉ)፡፡ መላእክትን በእውነት (በቅጣት) እንጂ አናወርድም፡፡ ያን ጊዜም የሚቆዩ አይደሉም፡፡ እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡ ከአንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልክተኞችን) በእርግጥ ልከናል፡፡ ማንኛውም መልእክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ኾነው እንጅ አይመጣቸውም ነበር፡፡ እንደዚሁ (ማስተባበልን) በአመጸኞቹ ልቦች ውስጥ እናገባዋለን፡፡ በእርሱ አያምኑበትም፡፡ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች፤ (እንደጠፉ ይጠፋሉ)፡፡ በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ፤ «የተዘጉት ዓይኖቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን» ባሉ ነበር፡፡ በሰማይም ላይ ቡርጆችን በእርግጥ አድርገናል፡፡ ለተመልካቾችም (በከዋክብት) አጊጠናታል፡፡ ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል፡፡ ግን (ወሬ) መስማትን የሚሰርቅ ወዲየውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል፡፡ (ያቃጥለዋል)፡፡ ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልናባት፡፡ በውስጧም (የተለካን) በቃይ ሁሉ አበቀልንባት፡፡ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልኾናችሁትንም (እንስሳትን) አደረግንላችሁ፡፡ መካዚኖቹም (መክፈቻቸው) እኛ ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደውም፡፡ ነፋሶችንም (ደመናን) ተሸካሚዎች አድርገን ላክን፡፡ ከሰማይም (ከደመና) ዝናብን አወረድን፡፡ እርሱንም አጠጣናችሁ፡፡ እናንተም ለእርሱ አድላቢዎች አይደላችሁም፡፡ እኛም ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን፡፡ እኛም (ፍጡርን ሁሉ ) የምንወርስ (ቀሪ) ነን፡፡ ከእናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ወደ ኋላም ቀሪዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ጌታህም እርሱ ይሰበስባችኋል፡፡ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡ ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው፡፡ ጃንንም (ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡ ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡ እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ፡፡ (ፍጥረቱን) ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ፡፡ መላእክትም መላውም ተሰብስበው ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር፡፡ ከሰጋጆቹ ጋር ከመኾን እንቢ አለ፡፡ (አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ላንተ ምን ምክንያት አለህ» አለው፡፡ «ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም» አለ፡፡ (አላህ) አለው «ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡» «ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ፡፡» «ጌታዬ ሆይ! እንግዲውያስ (ሰዎች) እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ፡፡ (አላህም) አለ «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡ «እስከታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡» (ኢብሊስ) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ (ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡» «ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡» (አላህም) አለ «ይህ በእኔ ላይ (መጠበቁ የተገባ) ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» «እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡» «ገሀነምም (ለርሱና ለተከተሉት) ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ «ለእርሷ ሰባት ደጃፎች አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ «እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሰላም ግቧት (ይባላሉ)፡፡ «ባልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚቅጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡ «በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካቸውም፡፡ እነሱም ከእርሷ የሚወጡ አይደሉም፡፡» ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡ ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡ ከኢብራሂም እንግዶችም (ወሬ) ንገራቸው፡፡ በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን (አስታውስ)፡፡ (እርሱም) «እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን» አላቸው፡፡ «አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡ «እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ» አለ፡፡ «በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡ «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ፡፡ «እናንተ መልክተኞች ሆይ! ኧረ ለመኾኑ ነገራችሁ ምንድን ነው» አለ፡፡ «እኛ አመጸኞች ወደ ኾኑ ሕዝቦች ተልከናል» አሉት፡፡ «የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ፡፡ (እነርሱን) እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን፡፡ «ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷን (በቅጣቱ ውስጥ) ከሚቀሩት መኾኗን ወሰነናል» (አሉ)፡፡ መልክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ፤ (ሉጥ) «እናንተ የተሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡ «አይደለም እኛ ሕዝቦችህ በርሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንህ» አሉት፡፡ «እውነትንም ይዘን መጣንህ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡ ከቤተሰብህም ጋር በሌሊቱ ከፊል ኺድ፡፡ ከኋላቸውም ተከተል፡፡ ከእናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ፡፡ ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ» (አሉት)፡፡ ወደርሱም ያንን ትእዛዝ አወረድን፡፡ (እርሱም) የእነዚህ (ሕዝቦች) መጨረሻ ያነጉ ሲኾኑ (ሥራቸው) መቆረጥ ነው፡፡ የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ኾነው መጡ፡፡ (ሉጥም) አለ «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ፡፡ «አላህንም ፍሩ፤ አታሳፍሩኝም፡፡» «ከዓለማት (ማንንም እንዳታስተናግድ) አልከለከልንህምን» አሉት፡፡ (ሉጥም) «እነኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (አግቧቸው)» አለ፡፡ በዕድሜህ እንምላለን እነሱ በእርግጥ በስከራቸው ውስጥ ይዋልላሉ፡፡ ጩኸቲቱም ፀሐይ የወጣችባቸው ሲኾኑ ያዘቻቸው፡፡ ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ መገምገሚያዎች አሉበት፡፡ እሷም (ከተማይቱ) በቀጥታ መንገድ ላይ ናት፡፡ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለምእምናን መገሰጫ አለ፡፡ እነሆ የአይከት ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ፤ ከነሱም ተበቀልን ሁለቱም (የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች) በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው፡፡ የሒጅርም ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ ተዓምራታችንንም ሰጠናቸው፡፡ ከእርሷም ዘንጊዎች ነበሩ፡፡ ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ኾነው ይጠርቡ ነበር፡፡ ያነጉም ሲኾኑ ጩኸት ያዘቻቸው፤ (ወደሙ)፡፡ ይሠሩትም የነበሩት ሕንጻ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡ ሰማያትንና ምድርንም በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ (በላግጣ) አልፈጠርንም፡፡ ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት፡፡ መልካምንም ይቅርታ አድርግላቸው፡፡ ጌታህ እርሱ (ያልነበረን) ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡ ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ ከእነርሱ (ከከሓዲዎች) ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፡፡ በእነሱም ላይ (ባያምኑ) አትዘን፡፡ ክንፍህንም ለምእምናን አለዝብ፡፡ በልም «እኔ ግልጽ አስፈራሪው እኔ ነኝ፡፡» (ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (በኾነ ቅጣት አሰፈራሪያችሁ ነኝ በል)፡፡ (እነርሱም) እነዚያ ቁርኣንንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው፡፡ በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡ የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡ ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡ (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፡፡ በእርግጥም (ፍጻሜያቸውን) ወደፊት ያውቃሉ፡፡ አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መኾኑን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡ እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡ Prev Next 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind