29.The Spider 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም) ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን እነዚያንም ከእነሱ በፊት የነበሩትን በእርግጥ ፈትነናል፡፡ እነዚያንም እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ውሸታሞቹንም ያውቃል፡፡ ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጠረጥራሉን ያ የሚፈርዱት (ፍርድ) ከፋ፡፡ የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው (ይዘጋጅ)፡፡ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነውና፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ የታገለ ሰውም የሚታገለው ለነፍሱ ነው፡፡ አላህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና፡፡ እነዚያም ያመኑ፤ መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹን ሥራዎቻቸውን ከእነሱ ላይ እናብስላቸዋለን፡፡ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን፡፡ ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፡፡ ላንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን (ጣዖት) በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው፡፡ መመለሻችሁ ወደኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ እነዚያንም ያመኑ፤ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ በደጋጎቹ ውስጥ በእርግጥ እናገባቸዋለን፡፡ ከሰዎችም በአላህ አመንን የሚል ሰው አልለ፡፡ በአላህም (በማመኑ) በተሰቃየ ጊዜ የሰዎችን ማሰቃየት እንደ አላህ ቅጣት ያደርጋል፡፡ ከጌታህም እርዳታ ቢመጣ እኛ በእርግጥ ከእናንተ ጋር ነበርን ይላሉ፡፡ አላህ በዓለማት ሕዝብ ልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ አይደለምን አላህም እነዚያን ያመኑትን በእርግጥ ያውቃል፡፡ መናፍቆቹንም ያውቃል፡፡ እነዚያም የካዱት ሰዎች ለእነዚያ ላመኑት «መንገዳችንን ተከተሉ፤ ኀጢአቶቻችሁንም እንሸከማለን» አሉ፡፡ እነርሱም ከኀጢአቶቻቸው ምንንም ተሸካሚዎች አይደሉም፡፡ እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር (ሌሎች) ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ፡፡ በትንሣኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት በእርግጥ ይጠየቃሉ፡፡ ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው፡፡ ኑሕንና የመርከቢቱንም ጓዶች አዳናቸው፡፡ እርሷንም ለዓለማት ተዓምር አደረግናት፡፡ ኢብራሂምንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «አላህን ተገዙ ፍሩትም፡፡ ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለእናንተ በላጭ ነው፡፡ «ከአላህ ሌላ የምትገዝዙት ጣዖታትን ብቻ ነው፡፡ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፡፡ ተገዙትም፡፡ ለእርሱም አመሰግኑ፡፡ ወደእርሱ ትመለሳላችሁ፡፡ «ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል፡፡ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም፡፡» አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀመር ከዚያም እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡ «፡--በምድር ላይ ኺዱ፤ መፍጠርንም እንዴት እንደ ጀመረ ተመልከቱ፡፡ ከዚያም፤ አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና» በላቸው፡፡ የሚሻውን ሰው ይቀጣል፡፡ የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ እናንተም በምድርም ኾነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳትም ተከላካይም ምንም የላችሁም፡፡ እነዚያም በአላህ አንቀጾችና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ፡፡ እነዚያም ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ የሕዝቦቹም መልስ፡- «ግደሉት፤ ወይም አቃጥሉት» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ከእሳቲቱም አላህ አዳነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉበት፡፡ (ኢብራሂም) አለም «ከአላህ ሌላ ጣዖታትን (አማልክት) የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላቸሁ በከፊሉ ይክዳል፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፡፡ መኖሪያችሁም እሳት ናት፡፡ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም፡፡» ሉጥም ለእርሱ አመነ፤ (ኢብራሂም) «እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ፡፡ እነሆ እርሱ አሸናፊው ጥበበኛው ነውና» አለም፡፡ ለእርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፡፡ በዘሩም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍን አደረግን፡፡ ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው፡፡ ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡ «እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን» (አላቸው)፡፡ የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ» አለ፡፡ መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት፡፡ «በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ» አላቸው፡፡ «እኛ በውስጧ ያለውን ይበልጥ ዐዋቂ ነን፡፡ (እርሱን) በእርግጥ እናድነዋለን፡፡ ቤተሰቦቹንም ጭምር፡፡ ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት» አሉት፡፡ መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በእነሱ ምክንያት አዘነ፡፡ በእነርሱም ልቡ ተጨነቀ፡፡ «አትፍራ፤ አትዘንም፡፡ እኛ አዳኞችህ ነን፡፡ ቤተሰቦችህንም፤ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ ናት» አሉትም፡፡ «እኛ በዚህች ከተማ ሰዎች ላይ ያምጹ በነበሩት ምክንያት ከሰማይ ቅጣትን አውራጆች ነን፡፡» በእርግጥም ለሚያስቡ ሰዎች ከእርሷ ግልጽ ምልክትን ተውን (አስቀረን)፡፡ ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን (ላክን)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፣ የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ፣ በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ አላቸውም፡፡ አስተባባሉትም፡፡ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው፡፡ በሃገራቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡ ዓድንና ሰሙድንም (አጠፋን)፡፡ ከመኖሪያዎቻቸውም (ፍርስራሾች በኩል መጥፋታቸው) ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ፡፡ ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው፡፡ ከመንገድም አገዳቸው፡፡ የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ፤ (ግን አላስተዋሉም)፡፡ ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም (አጠፋን)፡፡ ሙሳም በተዓምራቶች በእርግጥ መጣባቸው፡፡ በምድርም ላይ ኮሩ፡፡ አምላጪዎችም አልነበሩም፡፡ ሁሉንም በኅጢኣቱ ያዝነው፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አልለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ያሰጠምንው አልለ፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡ የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡ አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚግገዙትን ማንኛውንም ያውቃል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን፡፡ ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎቹ አያውቋትም፡፡ «አላህ ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፡፡» በዚህ ውስጥ ለምእምናን ተዓምር አለበት፡፡ ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡ የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» እንደዚሁም ወዳንተ መጽሐፍን አወረድን፡፡ እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው፤ በእርሱ ያምናሉ፡፡ ከእነዚህም (ከመካ ሰዎች) በእርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ በተዓምራቶቻችንም ከሓዲዎቹ እንጂ ማንም አይክድም፡፡ ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፡፡ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር፡፡ አይደለም እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ ዕውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ (የጠለቀ) ግልጾች አንቀጾች ነው፡፡ በአንቀጾቻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም፡፡ «በእርሱ ላይም ከጌታህ ዘንድ ተዓምራቶች ለምን አልተወረዱም» አሉ፡፡ «ተዓምራቶች አላህ ዘንድ ብቻ ናቸው፡፡ እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ» በላቸው፡፡ እኛ መጽሐፉን በእነሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሳጼ አለበት፡፡ «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል» በላቸው፡፡ እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑ በአላህም የካዱ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎች ናቸው፡፡ በቅጣትም ያስቸኩሉሃል፡፡ የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር፡፡ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል፡፡ በቅጣት ያስቸኩሉሃል፡፡ ገሀነምም ከሓዲዎችን በእርግጥ ከባቢ ናት፡፡ ቅጣቱ ከበላያቸው፣ ከእግሮቻቸውም ሥር በሚሸፍናቸው ቀን ትሠሩት የነበራችሁትን ቅመሱ በሚላቸውም (ቀን ትከባቸዋለች)፡፡ እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ እኔንም ብቻ ተገዙኝ፡፡ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ከዚያም ወደኛ ትመለሳላችሁ፡፡ እነዚያም ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ከገነት በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የሠራተኞች ምንዳ ምንኛ አማረ (እነሱ) እነዚያ የታገሱ በጌታቸውም ላይ የሚመኩ ናቸው፡፡ ከተንቀሳቃሽም ምግቧን ለመሸከም የማትችለው ብዙ ናት፡፡ አላህ ይመግባታል፡፡ እናንተንም (ይመግባል)፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሲሳይን ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)፡፡ በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡ በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ (ያጋራሉ)፡፡ ወደፊትም (የሚጠብቃቸውን) ያውቃሉ፡፡ ሰዎቹ ከዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ (አገራቸውን ) ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን በውድቅ ነገር ያምናሉን በአላህም ጸጋ ይክዳሉን በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ይበልጥ በዳይ ማነው በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ የለምን እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡ Prev Next 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind